የአልሻባብ ሶስት ቁልፍ አመራሮች ተደመሰሱ

admin
0



የአልሻባብ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ኃላፊን ፏአድ መሐመድ ከሌፍ (ሼንጎሌ) ጨምሮ ሶስት የቡድኑ አመራሮች ተደመሰሱ። የአልሻባብ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ኃላፊን ፏአድ መሐመድ ከሌፍ (ሼንጎሌ) ጨምሮ ሶስት የቡድኑ አመራሮች መደምሰሳቸውን የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊና ጊዜያዊ የፀጥታ ኮማንድፖስት አስተባባሪ ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ተናገሩ።

ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ አክለውም፤ ባለፉት ጥቂት ቀናት ከኢፌዴሪ አየር ኃይል ጋር በመቀናጀት በተወሰደው ርምጃ የሽብር ቡድኑ ኢትዮጵያን ለማጥቃት ያዘጋጃቸውን የትጥቅና ስንቅ ዴፖዎች ማውደም ተችሏል፡ ያሉ ሲሆን፡ በተጨማሪም የአሸባሪ ቡድኑ አመራሮችና ታጣቂዎች በተወሰደው ርምጃ ተደምስሰዋል ብለዋል።

ከተደመሰሱት ውስጥ የአልሸባብ ከፍተኛ ኮማንደሮች ውስጥ:-

1. ፏአድ መሐመድ ከለፍ (ሼንጎሌ) የአልሸባብ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ሃላፊ፣

2.አብዱላዚዝ አቡ ሙሳ የአልሸባብ ቃል አቀባይ፣

3.ኡቤዳ ኑር ኢሴ የአልሸባብ የቦኮል ዞንና የኢትዮጵያ ድንበሮች አዋሳኝ ሃላፊ መደምሰሳቸውን ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ ለኢዜአ ገልጸዋል።

Post a Comment

0Comments
Post a Comment (0)
featured/opinion